Skip to main content

 የቢሮው ስልጣንና ተግባራት

  •   ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ የተመቻቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ያደርጋል፣

  •   በክልሉ ውስጥ ንግድን ለማስፋፋትና ለማጠናከር ቀልጣፋ የግብይት ስርዓትና ተገቢ የንግድ አሰራር እንዲሰፍን ያደርጋል፣

  •   አግባብ ባለው ህግ መሰረት የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፣ ይሰርዛል፣ የንግድ መዝገብ ያደራጃል፣ 

  •   በህግ በልዩ ሁኔታ ለሌላ አስፈፃሚ አካል የተሰጠው እንደተጠበቀ ሆኖ ህገ-ወጥ የግብርና ምርቶች ዝውውር ይቆጣጠራል፣ ይከታተላል፣ በህግ አግባብ እርምጃ ይወስዳል፣ 

  •   በህግ በልዩ ሁኔታ ለሌላ አስፈፃሚ አካል የተሰጠው እንደተጠበቀ ሆኖ የግብይት ሥርዓትን በበላይነት ይመራል፣ ይከታተላል፣ ድጋፍ ይሰጣል፣

  •   ተገቢ ያልሆነ የንግድ አሰራርን ለመከላከል የሚያስችል የተሟላ ስርዓት ይዘረጋል፣ የንግድ ህጎች መከበራቸውን ያረጋግጣል፣ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፣

  •   በሕግ መሰረት ለሸማቾች ጥበቃ ያደርጋል፣ የንግድ እቃዎችንና አገልግሎቶችን ሥርጭት ይቆጣጠራል፣

  •   አግባብ ባለው አካል የዋጋ ቁጥጥር የተደረገባቸውን መሰረታዊ የንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶች መተግበራቸውን ይቆጣጠራል፣

  •   አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ ያላቸው የንግድ እቃዎችና አገልግሎቶች የደረጃውን መስፈርት ማሟላታቸውን ይቆጣጠራል፣ ከተዘጋጀላቸው ደረጃ በታች ሆነው በተገኙት ላይ እርምጃ ይወስዳል፣

  •   የሀገሪቱን ህጋዊ ስነ-ልክ ስርዓት በአግባቡ መተግበሩን ይቆጣጠራል፣

  •   የንግድ፣ የዘርፍ እና የሙያ ማህበራት እንዲቋቋሙ ያበረታታል፣ የተቋቋሙትንም እንዲጠናከሩ ያደርጋል፣

  •   ንግድን በማስፋፋት ረገድ የከተማና የገጠር፣ የከተሞች የእርስ በርስ ትስስር እንዲጠናከር ስትራቴጂ ይቀይሳል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፣

  •   የኤግዚብሽንና ፕሮሞሽን ሥራዎችን በበላይነት ይመራል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣

  •   የግብርና ምርት ውጤቶች ጥራታቸው ተጠብቆ ተገቢውን ገበያ በአገር ውስጥና በውጭ እንዲያገኙ ያደርጋል፣

ዓላማውን ለማስፈፀም የሚችሉ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል።     .