የተቋሙ ዳራ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያክልል መንግስት አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባራት ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 195/2015 መሠረት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ እራሱን ችሎ እንዲቋቋም ሲደረግ ለቢሮው የተሰጡ የወል ተግባራት እንደተጠበቁ ሆነው የክልሉ ንግድ እንዲስፋፋ፣ እንዲዘምን እና ሕጋዊ አሠራር እንዲሰፍን፣ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ሥርዓት ስለመዘርጋት፤ የዋጋ ቁጥጥር ሊደረግባቸው የሚገቡ መሠረታዊ የንግድ ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን ዋጋ የማጥናት፣ የክልላችንን ሕጋዊ ሥነ-ልክና ተስማሚነት ሥርዓት ያላቸው ምርቶችን እና አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ ያላቸው የንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶች መስፈርት ማሟላታቸውን የመቆጣጠር፣ የሀገር ውስጥና የወጪ ምርቶች ገበያ ትሰስር የመፍጠር እና ከሸማቾች ጥበቃ አዋጅ የተሰጡትን ተግባራት በመስራት በንግድ አሰራሩ ላይ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን በማስተካከል ተገልጋዮችን ለማርካት በትኩረት እየሰራ ይገኛል።
የሴክተሩን ተልዕኮአንፃር የልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ የመልማትን አቅም በመገንባት የሰባት አመት ዕቅድ መነሻ በማድረግ በአመቱ የተጣሉ ግቦችን ለመፈጸም ጥረት ተደርጓል፡፡እንዲሁም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ትግባረ ተከትሎ ያለምንም ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የሚደረግ የዋጋ ጭማሪን ለመከላከል በየደረጃው ዋጋ የሚያረጋጋ ግብረ-ሀይል በማደራጀት እና የቅሬታና ጥቆማ መቀበያ ነጻ የስልክ መስመር 9348 በመዘርጋት ቁጥጥርና ክትትል ተደርጓል፡፡