የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ደንበኞች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት
ማለት በሕግ የተለዩትን የኢትዮጵያ የንግድ ፈቃድ መስጫ መደቦችን መሰረት ያደረገና የተገልጋዩን የአገልግሎት ጥያቄ በመቀበል በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ግልጽ፤ ተደራሽ፣ ፍትሃዊና ፈጣን በሆነ አኳኋን ንግድ ምዝገባና ፈቃድ የመስጠት፣ የንግድ ስም ስያሜ፣ የካፒታል ዕቃዎችንና የተቋም ዋስትናን የመመዝገብ አገልግሎቶችን ህጋዊና ተጠያቂነት ባለው አግባብ በአንድ ማዕከል የሚሰጥ አገልግሎት ነው፡፡
በዳይሬክቶሬቱ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች
1. ቅድመ ንግድ ሥም (የንግድ ድርጅት ሥም ምዝገባና ማጣሪያ)
- አዲስ ቅድመ የድርጅት ሥም ምዝገባና ማጣሪያ
- የድርጅት ሥም ማሻሻያ
2. የንግድ ምዝገባ
- አዲስ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት
- የንግድ ምዝገባ ምትክ
- የንግድ ምዝገባ ማሻሻያ
- የንግድ ምዝገባ ስረዛ
3. የንግድ ሥራ ፈቃድ
- አዲስ የንግድ ሥራ ፈቃድ ምስክር ወረቀት
- የንግድ ሥራ ፈቃድ እድሳት
- የንግድ ሥራ ፈቃድ ማሻሻያ
- የንግድ ሥራ ፈቃድ ምትክ
- የንግድ ሥራ ፈቃድ ስረዛ
4. የንግድ ሥም
- አዲስ የንግድ ሥም ምስክር ወረቀት
- የንግድ ሥም ማሻሻያ (ለውጥ)
- የንግድ ሥም ምትክ
- የንግድ ሥም ሥረዛ
ከላይ የተጠቀሱት በሚከተሉት ሕጋዊ አቋሞች ይሰጣሉ፡፡
1. ግለሰብ ነጋዴ
2. ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
3. የአክሲዮን ማህበር
4. የንግድ እንደራሴ
5. መንግስታዊ የልማት ድርጅቶች
6. የህብረት ሽርክና ማህበር
7. የንግድ ዘርፍ ማህበራት
8. መንግስታዊ ያልሆኑ የልማት ድርጅቶች
9. መንግስታዊ ያልሆነ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች