የንግድና ገቢያ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ቀመሪያ ረሻድ በቡታጅራ ከተማ አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በሴቶች የተመረቱ ምርቶችና አገልግሎት ለማስተዋወቅ የተዘጋጀው የንግድና ባዛር ኤግዚብሽን አስጀመሩ የካቲት 27/2017 ዓ.ም የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ በዓለም ለ114ኛ በሀገራችን ለ49ኛ ጊዜ "ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል!!!" በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የዘንድሮ የሴቶች ቀን/ማርች 8/ በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ይገኛል። በክብረ በዓሉ ላይ የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገቢያ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ቀመሪያ ረሻድ በምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ ቀኑን ምክንያት በማድረግ በሴቶች የተመረቱ ምርቶችና አገልግሎት ለማስተዋወቅ የተዘጋጀው የንግድና ባዛር ኤግዚብሽን አስጀመዋል። በክብረ በዓሉ ተሳታፊዎች ቀኑን በማስመልከት በቡታጅራ ከተማ በሴቶች ልማት ህብረት አባላት የተሰሩ የልማት ስራዎችን የመስክ ምልከታ እያደረጉ ይገኛል። በክብረ በዓሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወ/ሮ ፀጋነሽ ሀንጪሶ ፣የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶች ፌድሬሽን ፕረዘዳንት ወ/ፋጤ ተሰማ፣የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሴቶችና ህፃናት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ሲቲ ሙስጠፋ ፣የምስራቅ ጉራጌ ዞን ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ክብርት ወ/ሮ አለምፀሓይ ሽፈራው፣የዞን የሴት አመራሮች እና በዞኑ ውስጥ በሚገኙ የታችኛው መዋቅሮች የሴቶች ልማት ህብረት አባላት ተገኝተዋል።